የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ986 ሚሊዮን ብር የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ጀመረ።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ986 ሚሊዮን ብር የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት ጀመረ።

ፌዴራል ዋና ኦዲተር፣ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ለኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሦስት የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት የሚውል የ986 ሚሊዮን ብር ግዙፍ የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ወደ ሥራ አስገብቷል።

ለፌዴራል ዋና ኦዲተር፣ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን እና ለኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በጋራ አገልግሎት የሚሰጠው ይህ ፕሮጀክት፤ ሦስት ቤዝመንት እና ግራውንድ ጨምሮ ባለ ሦስት ፎቅ ዘመናዊ ሕንጻ፣ የ200 መኪኖች ማቆሚያ እና የቅጥር ግቢ ማስዋብ ሥራዎችን ያካተተ ነው።

ኢንተርፕራይዙ የገባውን ውል መሠረት በማድረግ፣ ዲዛይኑን ጨምሮ አጠቃላይ ግንባታውን በ7 ወራት አጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት አጠናቆ ለማስረከብ የሰው ኃይልና ማሽነሪዎቹን ወደ ሳይት በማሰማራት ሥራውን በቁርጠኝነት ጀምሯል።

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር እንዳልካቸው በዛብህ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆኑት የሳይት ዝግጅት፣ የወሰን ማካለል እና የአፈር ምርመራ ሥራዎች በተሳካ ሁኔታ በመከናወን ላይ ይገኛሉ።

ግንባታው ከመሬት በታች ሦስት ቤዝመንቶች ያሉት በመሆኑ፣ በዙሪያው ባሉ ይዞታዎችና መሠረተ ልማቶች ላይ ምንም ዓይነት አደጋ እንዳይደርስ የቁፋሮ ድጋፍ ግንባታ በልዩ ጥንቃቄ እየተከናወነ መሆኑን ኢንጂነር እንዳልካቸው ገልጸዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተጣለበትን አገራዊ ኃላፊነት ለመወጣትና ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በውል ስምምነቱ መሠረት በጥራትና በፈጣን አፈጻጸም ለማጠናቀቅ በከፍተኛ ትጋት እየሠራ ይገኛል።

Stay Updated with DCE News

Subscribe to our newsletter and never miss an update about our projects, achievements, and announcements.