ኢንተርፕራይዙ በድሬዳዋ ከተማ የገነባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፕሮጀክት ተመረቀ።

ኢንተርፕራይዙ በድሬዳዋ ከተማ የገነባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ፕሮጀክት ተመረቀ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል ግንባታን ከተሰጠው የውል ጊዜ ቀድሞ ያጠናቀቀው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ምስጋና ተችሮታል።

በድሬዳዋ ከተማ የተገነባው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የምስራቅ ፈጥኖ ደራሽ ማዕከል በዛሬው እለት በተመረቀበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥ ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝን በልዩ ሁኔታ አመስግነዋል።

ኢንተርፕራይዙ ለፕሮጀክቱ ከተሰጠው የውል ማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ግንባታውን ሙሉ በሙሉ በጥራት አጠናቆ ማስረከቡን በከፍተኛ አድናቆት የገለፁት ኮሚሽነር ጄኔራሉ የማዕከሉ ግንባታ ሳይጓተት የተጠናቀቀው፣ ያጋጠሙ የተለያዩ ማነቆዎችን በተግባር በመቅረፍ መሆኑን አብራርተዋል።

በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ለግንባታው የወጣው ወጪ ካለው አጠቃላይ የገበያና የኮንስትራክሽን ሁኔታ አንጻር እጅግ ወጪ ቆጣቢ መሆኑን ጠቅሰው፤ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ማዕከሉን ልክ እንደ ራሱ ተቋም በመቁጠር በጥራትና በከፍተኛ ቁርጠኝነት የገነባ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢንተርፕራይዙ በተመሳሳይ መልኩ በሐረር ከተማ የሚገኘውንና በቀጠናው ዘመናዊ የሆነውን የፖሊስ ሆስፒታል ግንባታ ወደ ማጠናቀቂያው ማድረሱንም ጠቁመዋል።
ማዕከሉ ድሬዳዋ ላይ መመስረቱ ለአካባቢውና ለአጎራባች የሐረሪና የሶማሌ ክልሎች ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ዋስትና የሚሰጥ መሆኑን የገለጹት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው፣ ግንባታው በጥራትና በተያዘለት ጊዜ መጠናቀቁ ለቀጠናው ትልቅ ኩራት መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካሪነት ግንባታው የተከናወነውና ዛሬ በይፋ የተመረቀው ይህ ግዙፍ ማዕከል የአስተዳደር ቢሮ ህንጻ፣ ደረጃቸውን የጠበቁ የሴቶችና የወንዶች ዶርሚተሪዎች፣ ክሊኒክ፣ የእንግዳ ማረፊያ እንዲሁም ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን ያካተተ ነው።

Stay Updated with DCE News

Subscribe to our newsletter and never miss an update about our projects, achievements, and announcements.